Association for Human Rights in Ethiopia

  • About
  • Key Resources
  • Publications
  • Archives
  • Contact Us
  • Ethiopia: Killings, arrests under new State of Emergency
  • Ethiopia arrests 30 journalist, bloggers and activists
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Facebook

Powered by Genesis

You are here: Home / Home / በትግራይ ክልል ከጦርነት ማግስት በዜጎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መንግስታዊ ትኩረትን ይሻሉ!!

በትግራይ ክልል ከጦርነት ማግስት በዜጎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መንግስታዊ ትኩረትን ይሻሉ!!

22nd March 2021 by Admin

ጋዜጣዊ መግለጫ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ሰፊ የሆነ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አለመሟላት በዜጎች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ድርጅታችንን እጅጉን ያሳስበዋል፡፡ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ  ምንም እንኳን በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ ጉዳይ ቢሆንም በጦርነቱ ከደረሰው ሰፊ ጉዳት ጋር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ አለመሆኑን የተለያዩ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። በጦርነቱ እና ጦርነቱን ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ በተከሰተው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል  የተነሳ በርካታ ዜጎች ለአስከፊ የሰብአዊ መብት ቀውስ መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ የበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ዘገባዎች ያረጋግጣሉ፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ድጋፍ ሰጪ አካላት እና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ባወጧቸውም ዘገባዎች እና ሰፊ የዳሰሳ መግለጫዎች መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እርምጃዎች እንዲወስድ በመወትወት ላይ ይገኛሉ።

በሌላ ኩነት ደግሞ በማናቸውም አካላት የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች እና ህጋዊ ያልሆኑ እርምጃዎች ትኩረት ሊሰጣቸው፣ እርምት ሊደረግባቸው እንዲሁም ዜጎች አስተማማኝ ጥበቃ ሊደረግላቸው እና አጥፊዎች ለህግ እንድቀርቡ ማድረግ ይገባል፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ክልል የሚገኙ ንጹሃን ዜጎች የመንቅሳቅስ እና የደህንነት ጉዳይ ልዩ ትኩረትን ያሻል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ታጅበው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ የነበሩ ተማሪዎች  የካቲት 11/2013 በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ስድስት ተማሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን እና ብዙዎች መቁሰላቸውን ተዘግቧል፡፡ 

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የተከሰተውን  የሰብአዊ ቀውስ ለማስተካከል በሚደረገው እርብርብ የሚሳተፉ ድርጅቶች ትኩረት በሚፈልጉ ቦታዎች ላይ ለመድረስ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና ፈቃዶችን እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን መንግስት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርቡ አዎንታዊ ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የሰብአዊ ቀውሱን ለመቆጣጠር እና ዜጎች ጊዜውን የጠበቀ እገዛ ያገኙ ዘንድ መንግስት ጥያቄዎችን በአዎንታዊ እና ፈጣን በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲሰጥ እንመክራለን፡፡

በተጨማሪም በዚሁ ክልል በሴቶች ላይ አስከፊ የሆነ ፆታዊ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የካቲት 04/2013 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎቸ ጦርንቱ በተጀመረ ሁለት ወራት ብቻ 108 ፆታዊ ጥቃቶች መመዝገባቸውን ያወጣ ሲሆን እነዚህ ድርጊቶች የበርካታ ንፁሃን ሴቶችን ህይወት የሚያጨልሙ እና መሰረታዊ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያስከትሉ በመሆናቸው ድርጅታችንን ያሳስበዋል፡፡

በመሆኑም ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች  በኢትዮጵያ፤ መንግስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመፍትሔ  እርምጃዎች እንዲወስድጥሪ ያቀርባል፡-

  • በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ ዜጎች ለሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ወይም አለመፈፀሙን በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በጉዳዩ ተሳትፎ የነበራቸው አካላት ለህግ የሚቀርቡበትንንና ተጎጂ ዜጎች ተገቢውን ካሳ የሚያገኙበትን ሁኔታ መንግስት እንዲያመቻች፤
  • በክልሉ የተከሰተውን የሰብአዊ ቀውስ እልባት እንዲሰጥ እና በዚሁም እገዛ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥር፤
  • በክልሉ የሚኖሩ ዜጎችን እና በህይወት የመኖር፣ የንብረት ጥበቃ እና በሰላም የመንቀሳቅስ ዋስትና እንዲሰጥ፤
  • በክልሉ ውስጥ ለሚንቅሳቀሱ እና ለጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ዜጎች የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አስትማማኝ ጥበቃ እንዲያደርግ
  • በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን በአስቸኳይ እንድያስቆም እንድሁም የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ተገቢውን እርዳታ እና እገዛ እንዲያገኙ እንዲሁም የጥቃቱ ፈጻሚዎች ለህግ እንዲያቀርቡ እንድያደርግ ስበስብ ለሰብአዊ መብቶች ያሳስባል፡፡
Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

Subscribe

Sign up to receive email updates

Previous Posts

የዜጎች ማንነትን መሰረት አድርገው ጥቃት እየፈፀሙ የሚገኙ ግለሰቦችንና ቡድኖችን መንግስት በህግ ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማንነት መሰረት አድርገው የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶቸን መንግስት ሊያስቆም ይገባል!!!

The government must stop the repeated identity-based attacks occurring in Benishangul-Gumuz Zone!

AHRE’s statement for the 72th Human Rights Day

በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እና በዜጎች ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል!!!

The humanitarian crisis of the war and ethnic-based attacks on the identity of citizens must be addressed!!!