Association for Human Rights in Ethiopia

  • About
  • Key Resources
  • Publications
  • Archives
  • Contact Us
  • Ethiopia: Killings, arrests under new State of Emergency
  • Ethiopia arrests 30 journalist, bloggers and activists
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Facebook

Powered by Genesis

የመስከረም ወር 2013 ዓ/ም ጋዜጣዊ መግለጫ

12th October 2020 by Admin

ጥቅምት 2 ቀን 2013 

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በመስከረም ወር 2013 ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ የተስተዋሉ ዋና ዋና ክስተቶችን መሰረት በማድረግ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቶል፡፡ 

በመተከል ዞን የደረሰ ጥቃት፤

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ እና ቡለን ወረዳዎች በጳጉሜ ወር 2012 ፣እንዲሁም ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ በመስከረም ወር 2013 በታጠቁ ቡድኖች ዘርን መሰረት ባደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች እንደተገደሉና እንደቆስሉ፤ ብሎም ንብረታቸው እንዲወድምባቸው ተደርጓል፣ ገሚሶቹም አካባባቢውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል፡፡ የአይን እማኞች እንደገለፁትና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎች እንዳረጋገጡት በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ሀይል ዜጎቹን የመጠበቅ ግዴታውን ሳይወጣ ቀርቷል፡፡ በመስከረም ወር የደረሰው ጥቃት የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በመሄድና የፀጥታ ኃይሉን በአካባቢው እንዳሰማራ ከገለፀ በኋላ መሆኑ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያሳይ ነው፡፡

በኮንሶ ዞን የተከሰተ ግጭት

በተመሳሳይም በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዪ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በግጭቱ ምክንያትም ከ5000 በላይ ነዋሪዎች ከጥቃት በመሸሸ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን በመስከረም ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ ከተከሰቱ አበይት የሰብአዊ መብት ጥሠቶች አንዱ ነበር፡፡

በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቁ ዜጎች

በሌላ በኩል ከ496ሺ989 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በጎርፍ አደጋ ምክንያት በአፋር፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሱማሌ ክልሎች ውስጥ ለጉዳት ተዳርገዋል።እንዲሁም 134ሺ889 ሰዎች መፈናቀላቸውን፣ በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ እና ዜጎች በተጠጋጋ ሁኔታ በካምፕ ውስጥ እንዲሰፍሩ በመደረጉ ለኮቪድ ወረርሽኝ በሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በአካባቢው የተንቀሳቀሱ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ስጋታቸውን በመግለጽ መንግስትን አሳስበዋል፡፡

የኃይማኖት ነጻነትን የሚጋፉ እርምጃዎች

የዜጎች የሀይማኖት ነፃነት ህገ-መንግስታዊ መሰረት ያለው መብት መሆኑ ይታወቀል፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ አንዳንድ ዞኖችና ወረዳዎች፣ በደቡብ ክልል በሆሳእና ከተማ የመስቀል በዓል ሀይማኖታዊ መሰረቱን ይዞ እንዳይከበር መሰናክል እንደተፈጠረባቸው አማኞች ገልፀዋል፡፡ በተለይም የኮቪድን በሽታ እንደከልካይ ምክንያት በማድረግ ገደብ መደረጉን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

የፍርድ ቤት ውሳኔን አለማክበር እና የዜጎችን የዋትና መብት መጋፋት

በመሰከረም ወር የተከሰተው ሌላው መሰረታዊ የመብት ጥሰት የፍርድ ቤት ውሳኔን ያለማክበር ሁኔታዎች ናቸው፡፡ በመሰረቱ የዋስትና መብት አላስፈላጊ እስራትን ለማስቀረት ወሳኝ የሆነ መብት ነው፡፡ በተለይም በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ዋስትና በማስያዝ እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ተጠርጣሪ ግለሰቡን በዋስትና ለመልቀቅ ፍቃደኛ ያለመሆን ሁኔታዎች ተስተውላል፡፡ የፍርድ ቤት ውሳኔን አለማክበር ለሰብአዊ መብቶች መከበር አደጋ ከመሆኑ በዘለለ እንደሀገር ለተጀመረው የፍትህ ስርአት ለውጥ አደጋ የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ መጣል

ግለሰቦች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ብሎም በሚፈልጉት ቦታ የመኖርና ንብረት ማፍራት በኢፌድሪ ህገ-መንግስታዊ መሰረት ያለው መብት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የመሰከረምን ወር ጨምሮ በተለያዩ ግዜያት መንገዶች ሲዘጉ ብሎም ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ ዜጎች ችግር ሲደርስባቸው ተስተውሏል፡፡ በተለይም ከባህር ዳር ወደ አዲሰ አበባ በሚጓዙ ተጓዦች ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የጉዞ መስተጓጎልና ገሚሶቹ መታወቂያቸው እየታየ ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተጓዦች በአቤቱታ መልክ ለተለያዩ ሚዲያዎች አቅርበዋል፡፡ ይህ ድርጊት ዜጎች በሀገራቸው ያላቸውን የመዘዋወር ነፃነት የሚገድብ ነው፡፡

ምክረ ሃሳቦች

በመሆኑም ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች  በኢትዮጵያ፤ መንግስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመፍትሔ  እርምጃዎች እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል፡-

  • የፊደራል መንግስትና የቤንሻንጉል ክልል ዘርን መሰረት ያደረጉ ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ ለዜጎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ የተፈናቀሉ ግለሰቦችን ወደቀያቸው እንዲመለሱ በማድረግ ለተጎዱ ዜጎች ተገቢውን ከሳ እንዲክሱ ፣ በተደጋጋሚ በአካባቢው ጥቃት የሚያደርሱ የታጠቁ ሀይሎች ላይ አስፈላጊ የሆነውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ አከባቢውን ከታጣቂ ሀይሎች ነፃ እንዲያወጡ እንዲሁም በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላት ወደ ህግ እንዲቀርብ በማድረግ በተሳትፎቸው ልክ በህግ ተጠያቂ እንዲደረጉ፣ 
  • መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለግጭቶች ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በአግባቡ በመለየት ግጭቶቹ ከመከሰታቸው በፊት የእርምት እርምጃ የሚወሰድበትን ስርአት በመዘርጋት በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ የእርስ በርስ ግጭቶችን ሊያስወግድ ይገባል፡፡ 
  • መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱ ያሉ የጎርፍ አደጋዎችን አስከፊ አደጋ እንዳያደርሱ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ሊደርስ የሚችለውን የሰብአዊ ቀውስ ሊቀንስ ይገባል፡፡ በተለይም ዜጎች ለኮቪድ  እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ሊያከናውን ይገባል፡፡
  • መንግስት በተለያዩ አከባቢዎች ቁጥራቸው አነስተኛ በሆኑ አማኒያን ላይ የሚደርስን  ጣልቃ ገብነተም ሆነ ተፅዕኖ ሊከላከል ይገባል፡፡ መሰረታዊ የሆነውን የዜጎች የሀይማኖት ነፃነት የሚገድቡ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር ሊኖር ይገባዋል፡፡ በተለይም የተለያዩ አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶችን በማንሳት ዜጎች በነፃነት የሚከተሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንዳይተገብሩ መሰናከል በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ የሆነ እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡
  • የፍርድ ቤትን ውሳኔ ማክበር ለሰብአዊ መብቶች መከበር እጅግ ወሳኝ ነገር በመሆኑ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት የተፈቀደላቸውና አስፈላጊውን የዋስትና ሁኔታ ያሟሉ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል፡፡ በመሆኑም የፍርድ ቤት ውሰኔ እንዳይፈፀም መሰናክል የሚፈጥሩ የመንግስት አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራርን መንግስት እንዲመሰረት፡፡
  • የግለሰቦችን ከቦታ ወደ  ቦታ መዘዋወር የሚገድቡ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርግ፣ ተገቢውን ክትትል በማድረግ የዜጎችን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ በመገደብ በዜጎች ላይ እንግልትና እንዳይደርስ በአፅኖት እናሳስባለን፡፡

Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

የነሐሴ ወር 2012 የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ

10th September 2020 by Admin

ጋዜጣዊ መግለጫ

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በነሐሴ ወር በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ የተስተዋሉ ዋና ዋና ክስተቶችን መሰረት በማድረግ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶል፡፡ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ 

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በነበረው ግጭት የንፁኃን ህይወት ማለፉን በመንግስት አካላት፤ እንዲሁም በተለያዩ የመብት ተሟጋች ቡድኖች ተገልፆል፡፡ አንዳንዶችም የፀጥታ ኃይሉ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ በመውሰዱ ምክንያት ለብዙዎች ሞት እና ለብዙዎች አካል መጉደል መንስኤ ሊሆን እንደቻለ ዘግበዋል፡፡  

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ለተቃውሞ በተጠሩ ሰልፎች ለመሳተፍ ወደ አደባባይ በወጡ ግለሰቦች እና በፀጥታ ሀይሎች መካከል በተከሰተው ግጭት ምክንያት የሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የፀጥታ ሀይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ጥሪውን አቅርቦል፡፡ 

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው የሰላም መደፍረስ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማጥናት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያደረገው ጥረት የሚያበረታታ ቢሆንም እሰከአሁን ድረስ ሙሉ ሪፖርት ግን አልቀረበም፡፡ ነሐሴ 8 ቀን /2012 ዓ/ም የወጣው የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ መግለጫ እንደሚያመለክተው አሁንም ቢሆን ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች የጥቃቱ ኢላማ የሆኑ ዜጎች አሁንም የጥቃት ስጋት ያለባቸው መሆኑን ከነዋሪዎቹ ያገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ስጋቱን ገልጿል ፡፡

ከዚህ ባሻገርም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጾ ታሳሪዎቹ በሚገኙባቸው አንዳንድ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ  እስር ቤቶች ውስጥ  አሳሳቢ የሆኑ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች መስተዋላቸውን በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ 

በሀገሪቱ የኮቪድ 19 መከሰት ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የህዘብን መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች፤ በተለይም የመሰብሰብ ነጻነትን  በከፋ ሁኔታ የሚገድብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የአዋጁ አተገባበር ወጥነት የጎደለው በመሆኑ የተነሳ በተለያዩ አካላት ቅሬታዎች እየቀረቡ መሆኑን ታዝበናል፡፡ በተለይም በመንግስት አካለት የሚጠሩ እና የሚዘጋጁ ስብሰባዎች ያለ ምንም እንቅፋት  ቁጥሩ ብዙ የሆነ ህዝብ እየተሳተፈ በመካሄድ ላይ ሲሆኑ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎች አካለት በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጠሩ የጋዜጣዊ መግለጫ እና ስብሰባዎች አጥጋቢ ያልሆኑ ምክንያቶች እየተሰጡ በጸጥታ ኃይሎች እንዲስተጓጎሉ መደረጉን እና በመንግስት በኩል የተወሰደው እርምጃም ተገቢ አለመሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች  በኢትዮጵያ፤ መንግስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመፍትሔ  እርምጃዎች እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል፡-

  • የክልል እና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች የህግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ ያላቸውን ሚና እና የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቅጡ በመረዳት  በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን በሚገልጹ ወይም የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ዜጎች ላይ  የፀጥታ ኃይሎች ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ እንዳይወስድ መንግስት ተገቢውን ክትትልና ጥንቃቄ እንዲያደርግ፤ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃዎች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ እና ያልተመጣጠነ ኃይል በሚጠቀሙ የፀጥታ አካላት ላይ ተገቢ እርምት መውሰድ ይኖርበታል፡፡የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስታት በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች እና በደረሱት ጉዳቶች ላይ በቂ እና አፋጣኝ ምርመራ በማካሄድ የምርመራቸውን ውጤት እና የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ፣
  • የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች  ለዳግም ጥቃት ስጋት ያለባቸው ነዋሪዎችን መንግስት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ እንዲሁም የጥቃት ማስፈራሪያ እና ዛቻዎችን በሚያደርሱ ቡድኖች ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ አርምጃ እንዲወስድ፣
  • በኦሮሚያ ከተከሰተው የሰላም መደፍረስ ችግር ስፋት አንፃር የእስር ሁኔታን በሚመለከት የመንግስት አቅም ውስንነት እንዳለ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች  በኢትዮጵያ የሚገነዘብ ቢሆንም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች የአያያዝና ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ችላ ሊባል አይገባም፡፡ በመሆኑም መንግስት በተቻለ አቅምና ፍጥነት እነዚህን ችግሮች እንዲፈታ፣
  • የኮቪድ 19 መከሰት ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አፈፃፀም  ያለ ምንም አድሏዊ አሰራር በመንግስት አካለትም ሆነ በሌሎች አካላት መካከል፤ በተለይም በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበራት ላይ በእኩልነት ተፈጻሚ እንዲሆን እና የዜጎችን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

Human Rights situation in Ethiopia in August 2020

10th September 2020 by Admin

Press Statement

September 10, 2020

Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) has issued this press statement on the basis of the major human rights situations in August 2020. AHRE is deeply concerned about the human rights situations in Ethiopia.

Government officials and several Human Rights defenders have confirmed that many civilians have been killed and injured in Wolita zone of the southern Nations, Nationalities and people’s region (SNNRP) in protests erupted following the request to establish separate statehood. As some reported, the use of excessive force by security forces has resulted in many deaths and injuries.

On the other hand, in the Oromia region, people lost their lives as a result of clashes between protestors and security forces. On a press statement released August 20, 2020 the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) called out for security forces to comply with their obligations and avoid using excessive force against protestors. 

Despite EHRC’s encouraging attempt to investigate the breach of peace and human rights violations that resulted from the murder of singer Hachallu Hundessa, a full report on the matter has yet to be given. A statement released on August 15, 2020 by the Commission noted that in some parts of Oromia, victims were still at risk of violence based on information received from the residents.

The statement further added that a large number of people have been apprehended and detained in prisons found in different parts of the Oromia region. The Commission also expressed deep concerns over human rights violation and treatment in some of these prisons. 

Following the outbreak of COVID-19 in the country the Ethiopian government has declared a state of emergency which is expected to limit basic human rights specially the right to public gatherings. However, Association for Human Rights in Ethiopia observed complaints from various parties about the inconsistency in the implementation of rules.  Several political parties called out the actions of the government to be unfair and partial concerning measures taken in off-putting press releases and meetings called by other bodies, especially political parties while meetings organized by the government faced no restrictions.

Therefore, Association for Human Rights in Ethiopia urges the authorities to:

  • Make sure that security forces comply with the standards of the rule of law and their responsibilities to serve and protect people and exercise the utmost restraint to avoid using excessive force on protestors who are acting within their rights.
  • We also urge authorities to carry out impartial investigations and prosecute those responsible for abuses and allow victims and their families to receive due justice.
  • We urge Ethiopian Human Rights’ Commission, Federal and Regional governments must conduct impartial and prompt investigation on allegations of abuses and notable excessive use of force and provide public reports on the results of their investigations and undertaken measures on those responsible.
  • Provide adequate protection to prevent further assaults on victims living in some parts of Oromia where the prior attacks took place following the assassination of Artist Hachallu Hundessa and take appropriate legal actions against groups that are carrying out threats and intimidations.
  • Given the gravity of the unrest, Association for Human Rights in Ethiopia understand the limitations on the capacity of the government on the context of the Oromia Crisis. However, the treatments and basic rights of detainees should not be neglected. Therefore, we ask the authorities to resolve these issues with urgency.
  • The implementation of the state of emergency following the outbreak of Covid-19 in the country should be carried out without any discrimination. We ask authorities to resolve impartial treatments against other bodies, specially opposition parties and civic societies and urge that fundamental rights and freedoms of citizens to be fully implemented.

Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

  • « Previous Page
  • 1
  • …
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • …
  • 29
  • Next Page »

Subscribe

Sign up to receive email updates

Previous Posts

The government must hold accountable individuals and groups who are committing identity-based attacks on citizens.

የዜጎች ማንነትን መሰረት አድርገው ጥቃት እየፈፀሙ የሚገኙ ግለሰቦችንና ቡድኖችን መንግስት በህግ ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማንነት መሰረት አድርገው የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶቸን መንግስት ሊያስቆም ይገባል!!!

The government must stop the repeated identity-based attacks occurring in Benishangul-Gumuz Zone!

AHRE’s statement for the 72th Human Rights Day

በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እና በዜጎች ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል!!!