Association for Human Rights in Ethiopia

  • About
  • Key Resources
  • Publications
  • Archives
  • Contact Us
  • Ethiopia: Killings, arrests under new State of Emergency
  • Ethiopia arrests 30 journalist, bloggers and activists
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Joint civil society letter to Ethiopian Prime Minister-designate on recent arrests of journalists and human rights defenders
  • Facebook

Powered by Genesis

The government must stop the repeated identity-based attacks occurring in Benishangul-Gumuz Zone!

10th January 2021 by Admin

Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is releasing this press statement on the basic of the key human rights developments in Ethiopia on November, 2020.

Association for Human Rights in Ethiopia is concerned about the recurring identity-based attacks on civilians that are happening in the country. Specially:
According to reports from various sources, the ongoing racial violence has claimed many lives and injured many more.
On November 2012 hundreds of people were killed and injured, and thousands were displaced as a result of repeated racial violence. In addition, a bus carrying a large number of people from Bulen to Chagni was also attacked in the Kido neighboring, attacking several people, killing most of them dead. According to several victims and witnesses, these attacks are followed by horrific and inhumane acts.

Although it has been several months since the launching of a command post in the area consisting of the Defense Forces and the Federal Police to put the unrest in the area under control, attacks on residents have continued.
According to the internally displaced people in different Kebeles of Metekel Zone such as Chancho Kebele, Daliti Kebele, Albasa Kebele, Gedere Kebele for several weeks thousands of residents have been misplaced and are in dire conditions.

Similarly, victims and eyewitnesses told medias that many were killed and their property destroyed as a result of the attacks by the OLF militia in the Welega area of Oromia Region. Although the Federal as well as the Oromia Regional government claim to be taking measures against the groups, the armed groups continue to attack innocent civilians.
On the other hand, although the Federal Government in its “law enforcement” campaign has taken control of all towns in Tigray, including Mekelle, reports from local residents and aid groups indicate that there is a serious humanitarian crisis in the area due to severe infrastructure caused by the war.
Association for Human Rights in Ethiopia urges the government and concerned parties to take the following remedial measures:

  • Ethnic based attacks are major cause of loss of civilians lives therefore, must be addressed by the government immediately. In particular, the government must stop the ongoing violence in Benshangul Gumz region, Metekel Zone once and for all.
  • In particular, we urge the international community to pay attention to the inhumane and horrific human right abuses taking place in the Benihangul-Gumz region.
  • We urge the Federal and state governments to stop the attacks on innocent civilians by armed groups and for those responsible to be held accountable. We also urge immediate assistance and support for the displaced citizens.
  • The government must provide urgent repairs to the infrastructures destroyed following the Government’s law enforcement operation as they are affecting the lives of residents as well as work with aid agencies to provide emergency supplies to the affected population as soon as possible.
Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

AHRE’s statement for the 72th Human Rights Day

11th December 2020 by Admin

Recover better- stand up for Human Rights

“There can be no peace without development, no development without peace, and no lasting peace or sustainable development without respect for human rights and the rule of law.” Former UN Deputy Secretary-General Jan Eliasson
For Ethiopians, COVID-19 has been most devastating. Its eruption has been followed by grave human rights violations in different parts of the country. A number of innocent citizens died, wounded, lost their properties and displaced from their home towns due to ethnic based attacks. A number of
precautionary measures taken by the government, including the extension of the 6th national election that disappointed prominent oppositions, have contributed for the most human rights violations and chaos occurred in the country.
No peace in most part of the country where ethnic based attack is prevalent. The human rights violations have continued, and people are being brutally killed and displaced. On the other hand, development can never be achieved without peace and there can be no peace and security without respect for human rights and rule of law. Ethiopians are struggling to recover from COVID-19 and unrest that followed its eruption.
Hence, upon celebrating the 72th year of Human Rights Day, AHRE calls up on all the concerned parties to stop the massive human rights violations happening in different parts of our country and ensure rule of law, and thereby secure the safety and security of citizens dwelling at every corner of the country.

Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እና በዜጎች ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል!!!

10th December 2020 by Admin

ጋዜጣዊ መግለጫ

ባሳለፍነው ወር በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ የተስተዋሉ ዋና ዋና ክስተቶችን እና የመብት ጥሰቶች ላይ መሰረት በማድረግ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ 

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ባወጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች የዜጎችን ማንነት መሰረት አድርገው በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየደረሱ ያሉት ጥቃቶች እየተበራከቱ እና እየተባባሱ መሆኑን ገልጿል። በእነዚህ ጥቃቶችም ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ የጥቃት ሰለባ መሆኑን ሌሎች የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም በመግለጫዎቻቸው ስጋቶቻቸውንም ጭምት አክለው ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህ በእንዲህ እያለ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአገሪቱ የሰሜን ክፍል፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት የአገሪቱን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ አድርሶታል።

የትግራይ ልዩ ሀይል በክልሉ ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ጦር አባላት ላይ በካምፕ ውስጥ እያሉ ያደረሱባቸው አሰቃቂ ጥቃት ለዚህ ጦርነት መቀስቀስ ዋነኛ ምክንያት ቢሆንም በክልሉ መንግስት እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል የነበረው መሻከር እና በመግለጫዎች የተደገፈ መናቆሮች ወደ እርስ በርስ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አለም አቀፍ የግጭት አጥኚ አካላት ጭምር ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ህውሃት የሚመራው የክልሉ ልዩ ኃይል በመከላከያ አባላት ላይ ከወሰደው ድንገተኛ አሰቃቂ እርምጃ በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ማይካድራ በተባለ ሥፍራ ቁጥራቸው ወደ አምስት መቶ የሚጠጉ ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ ተገድለው መገኘታቸውን ከመንግስት እና ከተለያዩ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል። ይህ በሰው ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በሌሎች ስፍራዎችም ቁጥሩ ይለያይ እንጂ ተደጋግሞ እየተፈጸመ መሆኑ ድርጅታችንን ክፉኛ አሳስቦታል።

በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ቁጥራቸው በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተፈናቀሉ መሆኑን እና እንደ አንዳንድ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባም ከሃያ ሺ በላይ የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ከግጭቱ በመሸሽ ወደ ሱድን እና ሌሎች አጎራባች አገሮች እየተሰደዱ መሆኑ ተገልጿል። በግጭቱ ሳቢያ መንገዶች በመዘጋጋታቸው እና የጸጥታውም ሁኔታ አስጊ በመሆኑ መሰረታዊ የሆኑ እንደ ምግብ እና የጤና አቅርቦቶች በሚፈለገው መጠን ለነዋሪው ሕዝብ ሊደርስ እንዳልቻለ እና በዚህም ሳቢያ የብዙ ሰዎች ሕይወት የከፋ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ድርጅቶች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

ከጦርነቱ መከሰት ቀደም ብሎም ሆነ በኋላ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች የተፈጸሙ ሲሆን ሲሆን በተለይም፡-

በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በ ጥቅምት 8 እና 9 ማንነታቸው ባልታወቀ አካለት በደረሰ ጥቃት ብዛት ያለቸው ዜጎች ማንነትን መሰረት ባደረገ ጥቃት ህይወታቸውን አጥተዋል፣ አካላቸው ጎድሎል፣ ንብረታቸው ወድሟል፡፡  ከቦታው እየወጡ ባሉት መረጃዎች ከአንድ ቤተሰብ ብቻ 4 እና 5 የቤተሰብ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ህፃናት፣ አረጋውያንና ሴቶች ጭምር የጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡

በተመሳሳይም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ማለትም በምዕራብ ሸዋ ዞን ምዕራብ ወለጋ እና በሆሩ ጉድሩ ዞኖች ማንነታቸው በግልፅ ባልታወቁ አካላት በሚወስዱት እርምጃ የሰላማዊ ሰዎች ህይወት በተደጋጋሚ መጥፋቱ ታውቆል፡፡ በተለይም በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዲላ ጎጎላ ታንታ ቀበሌ ታጣቂዎች በቀን 22/02 2013 በአካባቢው ኑሮቸውን መስረተው የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ የአካባቢው ነዋሪዎችን ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ በማለት በመጥረት በአሰቃቂ ሁኔታ በደረሰ ጥቃት ቁጥራቸው ከ40-60 ድረስ የሚደርሱ ንፁኃን ዜጎች ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደርጎል፡፡ ከዚህ ባለፈም ብዛት ያለቸው የአማራ ብሄር ተወላጆች በዚሁ ጥቃት ለአካል መጉደል መዳረጋቸው ተውቋል፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው ለጥበቃ የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለቅቆ በወጣበት ቀን መሆኑ በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ያመላክታል፡፡ ከጥቃቱ በሓላ በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ ዜጎች አሁንም ቢሆን የደህንነት ስጋት ያለባቸው መሆኑን በተደጋጋሚ ለተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ገልፀዋል፡፡

በአፋርና በሱማሌ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በተነሳ ግጭት ብዛት ያለቸው ዜጎችን ለሞትና  ለአካል ጉዳትና እንዲሁም መፈናቀል ዳርጎል፡፡ በተለይም በዚህ አካባቢ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ በሚነሳ ግጭት የብዙዎችን ህይወት አያጠፋ መሆኑ ይተወሳል፡፡

ከዘህ ባሻገርም ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በምሽት ሰአት ተጓዦች ላይ እና በአሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደርሶል በአንዳንድ አሽከርካሪዎች ላይም የአካል መጉደልና የህይወት መጥፋት አስከትሏል፡፡

የመሰብሰብ ነፃነትና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት መሰረታዊ የሰብአዊ መብትና በኢፊድሪ ህገመንግስትም በአንቀፅ 30 እውቅና የተሰጠው መሆኑ ይታወቀል፡፡ በጥቅምት ወር አብን የሚሰኘው ፓሪቲ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲወገዝ ለማድረግ የጠራው ሰልፍ እንዳይደረግ ተክልክሎል፡፡

በመሆኑም ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች  በኢትዮጵያ፤ መንግስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመፍትሔ  እርምጃዎች እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል፡-

  • በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአፋጣኝ እንዲገታ እና ለንጹሃን ዜጎች ሞትም ሆነ በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ጥቃት ያደረሱ እና ትዕዛዝ የሰጡ ሰዎች በቍጥጥር ስር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ፤
  • በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በመሸሽ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ እና ወደ ጎረቤት አገር የተሰደዱ ዜጎች በቂ ድጋፍ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው፤ እንዲሁም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ እና በመሰረታዊ አቅርቦት እጥረት ህይወታቸው ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎች የሰብአዊ እርዳታ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲደርሳቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ፤ 
  • የፊደራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልል ዘርን መሰረት ያደረጉ ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ ለዜጎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ፣ የተፈናቀሉ ግለሰቦችን ወደቀያቸው እንዲመለሱ በማድረግ ለተጎዱ ዜጎች ተገቢውን ከሳ እንዲክሱ ማድረግ፣ ከዚህ ባሻገር ዘርን መሰረት በማድረግ በየአካባቢው በሚደረጉ ጥቃቶች ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳትፎ ያላቸው አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ በተሳትፎቸው ልክ በህግ ተጠያቂ እንዲደረጉ፣ 
  • ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳሳሰብነው መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለግጭቶች ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በአግባቡ በመለየት ግጭቶቹ ከመከሰታቸው በፊት የክትትል ስርአት በመዘርጋትና የእርምት እርምጃ በማዘጋጀት በሀገሪቱ በተለያዩ ግዜያት የሚከሰቱ የእርስ በርስ ግጭቶችን ሊያስወግድ ይገባል፡፡ 
  • በሱማሌና አፋር ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ከማንነትና ከቦታ ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ በሚነሱ ጥቃቶች የሚደርሱ ግጭቶችን ለማስቀረት መንግስት የክልል መንግስታትንና ህዝቡን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ መፍትሔ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ 
  • የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በኢፊዲሪ ህገመንግሰት እውቅና የተሰጠውና በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ድጋፍ ያለው መብት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ምክንቶች መሰረት በማድረግ ይህንን መብት መገደቡ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰናክል በመሆኑ መንግስት የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶችን እያነሳ ቡድኖች የሚጠይቁትን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሊገድብ አይገባም፡፡
Share this articleShare on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter
Share on LinkedIn
Linkedin
Share on Tumblr
Tumblr
Email this to someone
email

Filed Under: Home

  • « Previous Page
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • …
  • 28
  • Next Page »

Subscribe

Sign up to receive email updates

Previous Posts

AHRE’s statement for the 72th Human Rights Day

በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እና በዜጎች ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል!!!

The humanitarian crisis of the war and ethnic-based attacks on the identity of citizens must be addressed!!!

Association for Human Rights in Ethiopia September 2020 Press release

የመስከረም ወር 2013 ዓ/ም ጋዜጣዊ መግለጫ

የነሐሴ ወር 2012 የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ